Welcome
Login / Register

About Marriage | ስለ ትዳር


 • ብዙ ትዳሮች ለምን ይፈርሳሉ ወይም ይብተናሉ?

  1. የተሳሳተ የትዳር ጓደኛ ምርጫ

  የማይሆነንን የትዳር ጓደኛ ካገባን ወይም ከያዝን በርግጥም የተዛባና ግራ የተጋባ ትዳር ይኖረናል።

  2. በተዘበራረቁና በደምብ ባልነጠሩ ምክንያቶች ላይ ተመስርተን ትዳር ስንይዝ

  ለምን ትዳር እንይዛለን? ስለ ተፋቀርን እና ስለተፈላለግን ነው ወይስ ውጫዊ በሆነ ሐይል ተገፍተንና ተገደን? ህብረተሰቡ የተጋቡን ስለሚያንቆለጳጵስ ነው? የተጋቡ የቅርብ ጓደኞቻችንን ለመምሰል ነው? ውይስ ሳላገባ እያረጀሁኝ ነው ከሚል እራሳችን ከፈጠርነው ሀሳብ በመነሳት ነው? ውይስ የአንድ ጊዜ ጥፋትን ለመሸፋፈን ወይም በስህተት ሳናስብበት ባጋጣሚ ልጅ ስላፈራን ነው የምንጋባው? በዛም አለ በዚህ ትክክለኛ ባልሆነ እና ተልካሻ በሆነ ምክንያት ከሆነ የተጋባነው፣ በርግጥም ትዳሩ ወይም እድሜ አይኖረውም አልያም ግጭት የበዛበትና ሰላም የራቀው ይሆናል።

  3. ትዳር የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰምበሌጥ ሲሆን

  በምንኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ አንዳንዴ፣ ነገሮችን መርምረንና አስበንበት ሰይሆን እንዲሁ በቶሎ ለማከናውንና ከችግሮቻችን በፍጥነት ለመውጣት ነው እምንታትረው። በዚህም ወደ ትዳር ዘለን ሳናስብ እንገባለን ለከፋ ችግርም እንጋለጠላን። ከፍቅር ጓደኞቻችን ጋር ማሳለፍ የሚገባንን ያማረ ጊዜ በደምብ ሳንጠግበውና ለትዳር የሚሆነንን የጠነከረ መሰረት ሳናበጅ እንገባበትና ሁሉንም ነገር ዝብርቅርቅ እናረገዋለን ደስታም ከትዳራችን ይርቃል።

  4. ከትዳር የምንጠብቃቸው ነገሮችን በደምብ አለመረዳት

  ከትዳር ምን እንጠብቃለን? በርግጥም ብዙ ነገር እንጠብቃለን። በዛ ልክም ግን ብዙ ተግዳሮቶችና ያልተጠበቁ ክስተቶች ይኖራሉ፤ ለምሳሌ የስሜት፣ የአካል፣ የገቢ፣ የወሲባዊ እርካታና የተለያዩ የማህበረሰባዊ እክሎችና ተግዳሮቶች ባልተጠበቀ አኳኋን የጋጥማሉ። ህነዚህ ነገሮች ያጋጥማሉ ብለን ሳናስብ ከትዳር ሁሌም በጎ በጎውን እንዲገጥሙንና በንደዚህ መልኩ እምናስብ ከሆነ ችግር ላይ ከመውደቃችን ባሻገር ለትዳር መፍረስ እንደ መንሲኤ እንሆናለን።

  5. ግልፅ ያልሆኑና ያልነጠሩ ትንንሽ የሚመስሉ ትልልቅ ነገሮች

  የትዳር ዐለም ውስጥ ከመግባታችን በፊት በኋላም ባሉ ጊዚያት አብረን ብዙ ቦታዎች ላይ ልናሳልፍ እንችላለን። ለምሳሌ በመዝናነትና በመገባበዝ፣ ቤተሰብ በመጠየቅና በማህበራዊ ኑሮ ተሳትፎ አብረን ግዚያችንን ልናሳልፍ እንችላለን። ታድያ በዚህን ጊዜ በጨዋታና በቁምነገሮች መሀከል ብዙ ነገሮችን ልንባባል ብሎም ልንቃቃርና ልንቀያየም እንችላለን። እንደመንሲኤ ከሚቆጠሩት አንኳር ነገሮችም እንደ የቢሄር ነክ ክርክሮች፣ የሀይማኖት፣ የፖለቲካ፣ የማህበረሰባዊና የተለያዩ የአመለካከት ልዩነቶች ላይ ያተኮሩ ክርክሮችና ውይይቶች በማስተዋል ካልተተገበሩ ዘላቂ ለሆኑ ጥሎችና ቅራኔዎች መንሲኤ ይሆናሉ። እነዚህንም በአትኩሮትና በብልሃት ሳናረግብና ከሥራቸው ሳናፀዳ ዘለን ትዳር ውስጥ ስንገባ እነዚህ እነደ ጥቃቅንና ትንንሽ አድርገን የፈረጅናቸው ነገሮች የኋኋላ ከመጠን በላይ ገዝፈውና ጎልብተው ሂወታችንን አዘበራርቀው ትዳራችንን እንድናፈርስ ያስገድዱናል።   

  6. ከህብረተሰቡ የሚመነጩ አሉታዊ ሂሶች

  አንዳንድ የማህበረሰቡ ክፍሎች ባንድም በሌላም  ምክንያት ተነሳስተው አዲስ የተጋቡት ባለትዳሮችን ግምት ውስጥ ያላስገባ የተለያዩ ትዳርን የሚያጥላሉና የሚያብጠለጥሉ ንግግሮችንና ተግባራትን ያከናውናሉ። ታድያ በዚህ መሀል ለትዳር ያለን እምነት ይሸረሸርና ትርጉምም እናጣበታለን መጨረሻውም መበታተን ይሆናል።

  7. ደካማ የመግባባት ክህሎት

  ትዳር ውስጥ መግባበትና ጥሩ የሆነ ሀሳብ የመግለፅና የመረዳት ክህሎት ማዳበር ያስፈልጋል።ይሄ ሳይሆን ቀርቶ ግን ሳንግባባና ሀሳብለሃሳብ ሳንገናኝ ከቀረን፣ ትዳራችን እርባና ቢስ ሆኖ መና ይቀራል።

  8. የቅርብ ጓደኛ ተፅኖ

  በትዳረ ዐለም ውስጥ የበጣም ቅርብ ጓደኛ ተፅኖ ካልተቆጣጠርነውና ልቅ ከሰደድነው፣ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኖ ትዳራችንን ለመበታተንና ለማፈራረስ እንደ መንስኤ ይሆናል።

  9. ችግርና ክፍተት በሚያጋጥሙበት ግዜ ምን ያህል እንተጣጠፋለን?

  የትዳርና የፍቅር ዐለም ውስጥ በርካታ መሰናክሎችና ተግዳሮቶች ያጋጥማሉ፤ በዚህን ጊዜ ከመሰናክሎቹ ጋር ምን ያህል እንተጣጠፋለን የሚለው ጥያቄ የትዳራችንን ህልውና ይወስነዋል።

  10. የዳበረ ግብረገብነት አለመኖር

  ትዳር ለዳበረና ጠንካራ ግብረገብነት ላላቸው እንጂ በሞራልም በግብረገብነትም ለላሸቁ ስብእና ለጎደላቸው ሰዎች አይሆኑም። እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ለትዳር አይመጥኑም አልያም አይሆኑም፤ ቢሆኑም በስብእና የበቁና የጎለበቱ ወላጆች ለሞሆን አይበቁም ትዳራቸውንም ማነኮታኮታቸው አይቀሬ ይሆናል።

  11. ስለራስ ብቻ ማሳብና መኖር

  ትዳር ውስጥ ስለ የጋራ ሁኔታዎችን ከማሰብ ውጪ  አንዱ ስለ ራሱ ብቻ የሚያስብ ራስ ወዳድ ከሆነ ትዳሩ ሳይውል ሳያድር መፈራረሱ ሳይታለም የተፈታ ይሆናል።

  12. ከትዳር ውጭ በፍቅር ወጥመድ ላይ መውደቅ

  በዚህ የተንቀሳቃሽ ስልኮችና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በበዙበት ዘመን ከትዳር አጋር ውጪ ለሆኑ የፍቅር ጨዋታዎች ቅርብና የተጋለጥን ሆነናል። በዚህን ጊዜ ከጊዝያዊ ስሜት ምክንያታዊነትን አጎልብተን ካልተገኘን በራሳችን ጊዜ ለትዳራችን መፍረስ መንሲኤ እንሆናለን።

  13. ሳንዘጋጅ ልጆች ሲኖሩን

  ልጅ ማፍራት እንደ ትልቅ ነገር የሚወሰድ ቁም ነገር ነው። ነገር ግን በደምብ ሳንዘጋጅና ለምን ልጅ ማፍራት እነዳስፈለገንና በደምብ ሳንግባባ ከሆነ፣ ልጅ ማፍራታችን የራሱ የሆነ ከፍተኛ ቀውስ በመፍጠር ሰለማዊ የነበረውን ትዳራችንን በመዘበራረቅ መቀመቅ ያዎርደዋል።

  14. ልጆችን ያለማፍራት

  ትዳር ውስጥ ልጆችን ማፍራትን ፈልግን ነገር ግን በተፈጥሮም ሆነ በሌሎች ሁኔታዎች ምክንያት ሳንችል ስንቀር፣ ትዳራችን ውስጥ ጥልቅ የሆነ መቃቃር ሊፈጥር ይችላል። በዚህን ጊዜ ብስጭታችንና መከፋታችን ምክንያታዊነታችንን ጋርዶት ጥፋቱ የአንዳችንም አለመሆኑ ሳንረዳና ሳናምን እንቀርና ትዳራችንን ገደል እንድንከት ይሆናል።

  15. የሐይማኖት ሚና

  በትዳር ውስጥ የሐይማኖት ነገር ምክንያታዊነት በገነነበት ሁኔታ ሳይታሰብበትና ሳንረዳው ካለፍነው፣ የኋላኋላ ከፍተኛና መጠነ ሰፊ የሆነ የማህበረሰባዊ መናጋትን ማስከተሉ አይቀሬ ነው። ከዚህም ባሻገር ትዳራችንን ለወቀሳና ለንዝንዝ በማጋለጥ እንዲፈራርስ ያደርጋል።

  16. ሚስጥር መደባበቅ ከመጣ

  በትዳር አጋሮች መሀከል ሚስጥር መደባበቅ ከፍተኛ የሆነ አለመግባበትን ሊፈጥር ይችላል። በተለይም ደግሞ በጣም አስፈላጊ በሆኑ ነገሮችና ሆን ተብሎ የተደረጉ የሚስጥር ክልከላዎች ከሆኑ፣ የኋላኋላ ግልፅ ይወጡና ለትዳራችን እድገትና ሰላም ማነቆ ይሆናሉ።

  17. ምክንያታዊ ያልሆነ ድብርት

  ትዳር ውስጥ ባልታወቁና በማይያዙና በማይጨበጡ ምክንያቶች ድብርት ሊመጣብንና ሊውጠን ይችላል። ታድያ በዚህን ጊዜ ቶሎ በመንቃት የተፈጠረውንና የተጋረጠብንን የድብርትና የመሰለቻቸት አደጋ ለማስወገድ ካልተጋን ትዳራችንን አደጋ ላይ ይጥለዋል።

  18. የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሚና

  ትዳር ውስጥ መሰረታዊ ከሚባሉት ቁልፍ ነገሮች፣ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት ዋነኛው መሆኑ አያጠራጥርም። በመሆኑም ትዳራችን ውስጥ በዚህ ቁልፍ ጉዳይ ላይ አንዱ ተጠቃሚና አንዱ ተጎጂ መሆን የለበትም። ስለዚህ ሁለቱም የትዳር አጋሮች ከወሲብ የሚያገኙትን እርካታ እኩል መሆን አለበት። ይሄ ሳይሆን ከቀረ ግን ከቤታችን ሰላመና ደስታ መራቃቸው አይቀሬ ይሆንና የትዳራችን አቅጣጫም ወደ መበተን ይሆናል።

  19. የትዳር አጋር ወላጆች ሚና

  በትዳራችን ውስጥ የዎላጆቻችን ሚና አስቀድመን ወሰንና ገደብ ካላበጀንለት ዞሮዞሮ እያደረ ጥልቅ ስንጥቅ ይፈጥርና ትዳራችን እንዲፈርስ የራሱ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርጋል።

  20. አለመገጣጠም

  አለመስማማት፣ አለመግባበትና በትንሹም በትሉቁም መነታረክና ባጠቃላይ በትዳር ሁኔታዎች አለመገጣጠም ካለና እየገነነ ከመጣ እየዋላ እያደረ ትዳራችንን ጠልፎ ይጥለዋል። በመሠረቱ ትዳር ውስጥ ከትዳር ጓደኛችን ጋር ያለን  የእውቀት አለመጣጣም፣ በስሜትና በወሲብ አለመገጣጠም እንዲሁም በሌሎች ነገሮች አለመረዳዳትና አለመጣጣም ካለ የትዳራችንን እጣ ፈንታ መበተንና መፈራረስ ይሆናል።

  21. ግጭቶች ሲኖሩ፣ እንዴት እንፈታቸዋለን

  በትዳር ሂዎት ውስጥ በርካታ አለመስማማቶች በርግጥ ይኖራሉ፣ የቀን ጎዶሎዎች ይኖራሉ፣ እንዲሁም የስሜት መቀያየሮችና መጥፎ አጋጣሚዎች ይኖራሉ። በዚህ ወሳኝ ጊዜ ታዳ ነገሮችን በማስተዋልና በብልሀት ካላለፍናቸው ትዳራችንን አደጋ ላይ ይጥሉታል።

  22. የገቢ ችግር

  ምንም እንኳ በትዳር ሂዎት ውስጥ ፍቅር ዋነኛው ቁልፍ ነገር ቢሆንም፣ ለንሮ የሚሆነን ገቢ መኖርና አለመኖር ትዳራችን እያበበና እየለመለመ እንዲሄድ ወይም በእንጭጩ ቀርቶ እንዲንኮታኮት የራሱን አስተዋፅኦ ያደርጋል።

  23. ሲበደል የኖረ ይበድላል እንዲሉ፣

  ሲበደል፣ ሲንቋሸሽና ሲከፋ የልጅነት ሙሉ እድሜውን የኖረ የትዳር ጓደኛ ተጊቢው የስነልቦናና የተለያዩ ባለሙያዎችን እገዛ ሳያገኝ ከሆነ በትዳር ውስጥ ለሚፈጠሩ ከፍተኛ መናቆር የተሞሉ አለመግባባቶችን እንደመንሲኤ ይሆናል። ከዚህም በዘለለ በትዳር ጓደኛ እና ትዳሩ ባፈራቸው ልጆች ሂዎት ላይ ከፍተኛና ዘላቂ የሆነ ጉዳት ያስከትላሉ።

  24. ትዳር ለጥቅም ፍለጋ ሲሆን

  አንዳንዴ ትዳር ጥቅም ፍለጋን ብቻ ሆኖ ይገኛል፤ ትዳር ድግሞ አንዱ በአንዱ ለመጠቀም በመፈለግ ሲሆን ከመጀመርያውኑ ትዳሩ ሻካራ ትዳር ይሆንና ብዙም ሳይዘልቅ ይፈራርሳል።

  25. እገዛ ስናጣ

  ትድር የተሳካ እንዲሆን ከቅርብ ወዳጅ ዘመድ ድጋፍና እርዳታን ይሻል። በተለይም ከእህት ወንድሞች፣ ከቅርብ ጓደኞች፣ እና ከተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ድጋፍ ያስፈልገዋል። በተለያዩ ምክንያቶች ይሄ ሳይሆን ሲቀር ግን ለትዳር መፍረስ ከፍተኛ የሆነ የራሱን ሚና ይጫወታል።

   

   *****ሙሉ የኢንግሊዘኛ ግልባጩን ከዚህ ሥር ባለው ሊንክ ማግኘት ይቻላል።

  Reference: https://www.capitalfm.co.ke/lifestyle/2017/05/25/why-so-many-marriages-fail-these-days-2/

   

  Read more »
RSS